ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ምፅዋት ከሰጪው ላይ መከራን ትከላከላለች እንጂ ገንዘቡን እንደማታጎድል፤ አላህ ለሰጪው ትልቅ መልካምን እንደሚተካለትና መመፅወቱ ጭማሪ እንጂ ጉድለት እንደማይሆን ገለፁ። መበቀል ወይም ባለቤቱን መቅጣት እየተቻለም ይቅር ማለት ኃይልና ልቅናን እንጂ አይጨምርም። አንድም ሰው ማንንም ፈርቶ፣ ለማስመሰልና ከሱ ጥቅም ፈልጎ ሳይሆን ለአላህ ፊት ብሎ አይተናነስምም ዝቅ አይልምም ምንዳው ልቅናና ከፍታ ቢሆን እንጂ።