explain-icon

ትንታኔ

ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ጂብሪል ለጎረቤታቸው ትኩረት እንዲቸሩ፣ ሐቁን እንዲጠብቁ፣ እንዳያውኩት፣ ለርሱ በጎ እንዲውሉ፣ በሚያደርስባቸው ጉዳት እንዲታገሱ ከማዘዝና ከመደጋገም እንዳልተወገደ ተናገሩ። ይህም ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ከጎረቤት ሀቅ ክብደትና ጂብሪል ይህን ትእዛዝ ከመደጋገሙ የተነሳ ከሞቱ በኋላ ትተውት የሚያልፉትን ገንዘባቸውን ለጎረቤታቸው እንዲሰጡ የሚያዝ ወሕይ ሊወርድ ይሆን ብለው እስኪያስቡ ደረሱ። ጎረቤት ሲባልም ሙስሊምም ሆነ ካፊር፣ ዘመድም ሆነ ባዳ ማንኛውም ለቤት ቅርብ የሆነ ማለት ነው።

explain-icon

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  • የጎረቤት ሐቅ ክብደትንና ይህንን መጠባበቅ ግዴታ እንደሆነ እንረዳለን።
  • የጎረቤት ሐቅ በአደራ መልክ መጠንከሩ ጎረቤትን ማክበርን፣ መውደድን፣ ለርሱ በጎ መዋልን፣ ከርሱ ጉዳትን መከላከልን፣ ሲታመም መጠየቅን፣ በደስታ ወቅት ማስደሰትን፣ በመከራ ወቅት ማፅናናትን ያስፈርዳል።
  • የጎረቤት ደጃፍ በቀረበ ልክ ሐቁም የጠነከረ ይሆናል።
  • ሸሪዓ ለጎረቤት በጎ መዋልና ከነሱ ላይ ጉዳትን መከላከልን የመሰለ ለማህበረሰቡ ጥቅም ያላቸው ድንጋጌዎችን ይዞ በመምጣቱ ረገድ የተሟላ መሆኑን እንረዳለን።