ከአቡ ዘር ረዲየሏሁ ዐንሁ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «የአላህ መልክተኛ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - እንዲህ ብለዋል: "አቡ ዘር ሆይ! መረቅ የቀቀልክ ጊዜ ውሃውን አብዛ! ጎረቤቶችህንም ተከታተል።"» ሶሒሕ ነው። - ሙስሊም ዘግበውታል።
explain-icon

ትንታኔ

ነቢዩ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- አቡ ዘር አልጚፋሪይን ረዺየሏሁ ዐንሁ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - መረቅ የቀቀለ ጊዜ ውሃውንና መረቁን እንዲያበዛና ከመረቁ ለጎረቤቶቹ በመላክም እንዲከታተላቸው አነሳሱት።

explain-icon

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  • ከጎረቤት ጋር መልካም በሆነ መልኩ በመኗኗር ላይ መነሳሳቱን እንረዳለን።
  • በጎረቤቶች መካከል ስጦታ መሰጣጠታቸው እንደሚወደድ እንረዳለን። ይህም ውዴታን ስለሚያመጣና ቅርርብን ስለሚጨምር ነው። ምግቡ የሚጣራ መአዛ ካለውና ጎረቤቶቹም እንደሚያስፈልጋቸው ከታወቀ ደግሞ ይህን ስጦታ መስጠት አፅንዖት የተሰጠው ጉዳይ ይሆናል።
  • ብታንስ እንኳ የገራልንን ጥሩን ነገር በመለገስ ላይና ለሙስሊሞች ደስታ ምክንያት በመሆን ላይ መነሳሳቱን እንረዳለን።