ከአቡ ሹረይሕ (ረዲየላሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እንዲህ አሉ፦ «"ወላሂ አላመነም! ወላሂ አላመነም! ወላሂ አላመነም!" "የአላህ መልክተኛ ሆይ ማን ነው?" ተባሉ። እርሳቸውም "ጎረቤቱ ተንኮሉን ያላመነው ሰው ነው።" አሉ።» ሶሒሕ ነው። - ቡኻሪ ዘግበውታል።
explain-icon

ትንታኔ

ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ማሉ። መሃላቸውንም ሶስት ጊዜ አድርገው አፅንዖት ሰጥተው እንዲህ አሉ: "ወላሂ አላመነም! ወላሂ አላመነም! ወላሂ አላመነም!" አሉ። ሶሐቦችም "የአላህ መልክተኛ ሆይ! ማን ነው ያላመነው?" አሉ። እርሳቸውም "ከክዳቱ፣ ከግፉና ከክፋቱ አንፃር ጎረቤቱ የሚፈራው ነው።" አሉ።

explain-icon

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  • ጎረቤቱ ከግፉና ከክፋቱ የማያምኑት ሰው ላይ ኢማን ውድቅ መደረጉ ትልቅ ወንጀል መሆኑንና ኢማኑ የጎደለው መሆኑን ይጠቁማል።
  • ለጎረቤት መልካምን በመዋል ላይና ጎረቤትን በንግግር ወይም በተግባር ማወክን በመተው ላይ ጠንካራ የሆነ ማነሳሳት መደረጉን እንረዳለን።