የአማኞች እናት ኡሙ ሰለማ ረዲየሏሁ ዐንሃ - አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና - አንድ ጊዜ ነቢዩ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- እንዲህ ሲሉ እንደሰማች አወሳች: አንድም መከራ የሚደርስበትና አላህ ለርሱ የመረጠለትን ይህንን ውዳሴ የሚል ሙስሊም የለም: {ኢና ሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂዑን} [አልበቀራ:156] ትርጉሙም {እኛ ለአላህ ነን እኛም ወደርሱ ተመላሾች ነን።} (አላሁመእጁርኒ) አላህ ሆይ! በደረሰበኝ መከራ የትእግስቴን ምንዳ ስጠኝ! (ፊ ሙሲበቲ) (ወአኽሊፍ ሊ ኸይረን ሚንሃ) ከርሱ የተሻለንም ለኔ ተካልኝ አይልም አላህ ለርሱ ከደረሰበት መከራ የተሻለን ቢለውጥለት እንጂ። ኡሙ ሰለማ እንዲህ አለች: አቡ ሰለማ የሞተ ጊዜ እንዲህ አልኩኝ: "ከአቡ ሰለማ የተሻለ ሙስሊም ከቶ ማን አለ? ወደ አላህ መልክተኛ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - በቅድሚያ የተሰደደ ቤተሰብ ነው። ከዚያም ግን አላህ አግዞኝ ይህንን ውዳሴ ተናገርኩት። አላህም ለኔ ከአቡ ሰለማ የተሻሉትን የአላህን መልክተኛ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ተካልኝ።"