explain-icon

ትንታኔ

ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም አላህ ወደ ሰዎች ቅርፅና ሰውነት ያምራል ወይስ አስቀያሚ ነው? ትልቅ ነው ወይስ ትንሽ? ጤነኛ ነው ወይስ በሽተኛ? በማለት እንደማይመለከት ገለፁ። ወደ ገንዘቦቻቸውም ብዙ ነው ወይስ ትንሽ? በማለት አይመለከትም። አላህ ባሮቹን በነዚህ ጉዳዮች ላይ ባላቸው መበላለጥ ተንተርሶ አይቀጣቸውምም አይተሳሰባቸውምም። ነገር ግን በቀልቦቻቸው ውስጥ ወዳለው ፍራቻ፣ የእምነት እርግጠኝነት፣ እውነተኝነት፣ ኢኽላስ (ፍፁማዊነት) ወይም የይዩልኝ ፣ የይስሙልኝ አስተሳሰብን ነው የሚመለከተው። ወደ ስራዎቻቸው ከመስተካከሏና ከመበላሸቷ አንፃር ይመለከትና በዛም መሰረት ይመነዳል።

explain-icon

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  • ቀልብን ከሁሉም ውግዝ ባህሪያት ማስተካከልና ማፅዳት ላይ ትኩረት መስጠት እንዳለብን እንረዳለን።
  • ቀልብ የሚስተካከለው በኢኽላስ ሲሆን ስራ የሚስተካከለው ደግሞ ነቢዩን ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም በመከተል ነው። አላህ ዘንድ ትኩረት የሚቸራቸውና ግምት ውስጥ የሚገቡት እነዚህ ሁለቱ ናቸው።
  • የሰው ልጅ በገንዘቡም፣ በውበቱም፣ በሰውነቱም ሆነ በዚህች ዓለማዊ መገለጫዎች በአንዳችም ነገር መሸወድ እንደሌለበት እንረዳለን።
  • ውስጣዊ ማንነትን ሳያስተካክሉ ውጫዊ የሆኑ መገለጫዎች ላይ ከመደገፍ መጠንቀቅ እንዳለብን ተረድተናል።