ለነቢዩ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - የሃዋዚን ምርኮኞች መጡላቸው። ድንገት ከነርሱ መካከል አንዲት ሴት ልጇን ትፈልግ ጀመር። አንድ ህፃን ስታገኝም ወተት በጡቷ ውስጥ በመጠራቀሙ ስለተጎዳች ትይዘውና ታጠባዋለች። ከምርኮኞች መካከልም ልጇን አግኝታ ያዘችውና ወደ ሆዷ አቅፋ ደግፋ አጠባችው። ነቢዩም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - ለባልደረቦቻቸው እንዲህ አሉ: "ይህቺ ሴትዮ ልጇን እሳት ውስጥ ትጥላለች ብላችሁ ታስባላችሁን?" እኛም "በራሷ ፍቃድ ማንም ሳያስገድዳት መቼም አትጥለውም።" አልናቸው። እርሳቸውም "አላህ ለሙስሊም ባሮቹ ይህቺ ለልጇ ካላት እዝነት የበለጠ እጅግ አዛኝ ነው።" አሉ።