ነቢዩ -የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- አላህ አንድን ትእዛዙን ታዛዥና ክልከላውን የሚርቅ አማኝ ባሪያውን የወደደ ጊዜ ጂብሪልን ይጣራል። አላህ እከሌን ይወደዋልና ውደደው። የመልአክቶች አለቃው ጂብሪል ዓለይሂ ሰላም ይወደዋል። ጂብሪልም ለሰማይ መልአክቶች ይጣራል። ጌታችሁ እከሌን ይወደዋልና ውደዱት። የሰማይ ነዋሪዎችም ይወዱታል። ቀጥሎ በአማኞች ቀልብ ውስጥ ለርሱ ውዴታን፣ ወደርሱ የመሳብንና በርሱ የመደሰትን ተቀባይነት እንዲኖረው ይደረጋል። አላህ አንድን ባሪያ የጠላ ጊዜም ጂብሪልን ይጣራል። እኔ እከሌን ጠልቼዋለሁና ጥላው። ጂብሪልም ይጠላዋል። ቀጥሎ ጂብሪል የሰማይን ነዋሪዎች ይጣራል። ጌታችሁ እከሌን ይጠላዋልና ጥሉት። እነርሱም ይጠሉታል። ከዚያም በአማኞች ቀልብ ውስጥ ለርሱ ጥላቻ እንዲኖር ይደረጋል።