ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም የሩቅን እውቀት አዋቂ ነኝ ባይ ጋር ከመሄድ አስጠነቀቁ። (ይህም ጠንቋይን፣ ኮኮብ እየተመለከቱ የሚተነብዩን፣ ጠጠርን ተንተርሰው የሚተነብዩንና የመሳሰሉትን የሩቅ እውቀትን ለመሞገት ለመነሻ ያህል የሚጠቀሙን የሚያጠቃልል የወል ስም ነው።) የሩቅን እውቀት አዋቂ ነኝ ባይ ጋር በመሄድ ሩቅ ከሆኑ ጉዳዮች መካከል አንዳችን መጠየቁ ብቻ በሱ ሳቢያ የአርባ ቀን የሶላቱን ምንዳ አላህ ይከለክለዋል። ይህም በዚህ ትልቅ ወንጀሉና ሀጢዐቱ ምክንያት መቀጣጫ እንዲሆነው ነው።