የአማኞች እናት የሆነችው ዓኢሻህ -አላህ መልካም ስራዋን ይውደድላትና- ስለነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ስነምግባር ተጠየቀች። ጠያቂውን ሁሉንም ምሉዕ ባህሪያት ወደ ሰበሰበው ወደ ተከበረው ቁርአን በመመለስ ጠቅላይ በሆነ ንግግር መለሰችለት። ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ቁርአናዊውን ስነምግባር የተላበሱ ፤ ቁርአን ያዘዘውን ይፈፅሙ፣ ቁርአን የከለከለውን ደግሞ ይርቁ እንደነበር፤ የሳቸው ስነምግባር በቁርአን መስራት ፣ ድንበሩ ላይ መቆም፣ የቁርአንን አዳብ መላበስ ፣ ምሳሌዎቹንና ታሪኮቹን ማስተንተን ነበር ብላ መለሰችለት።