የአላህ መልክተኛ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ዘንድ ሁለት ሰዎች ተወሱ። አንዱ ዓቢድ (አላህን አብዝቶ የሚገዛ) ሲሆን ሌላኛው ዐሊም (አዋቂ) ነው። ማንኛቸው ይበልጣል ተብለው ተጠየቁ። ነቢዩ የአላህ ሶላትና ሰላም በርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ አሉ፡ "የሸሪዓን እውቀቶች አውቆ በእውቀቱ ከመስራት አልፎ የሚያስተምር ሰው ማወቅ ያለበትን ግዴታዎች አውቆ ራሱን ለአምልኮ ብቻ ነፃ ካደረገ ሰው ጋር ያለው ልዩነት ነቢዩ -የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ከሶሓቦች ሁሉ ዝቅተኛ ከሆነው ጋር እንዳላቸው ልዩነትና ደረጃ ነው። ቀጥለውም ነቢዩ -የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- የዚህን ምክንያት እንዲህ በማለት ገለፁ። አላህ ሱብሓነሁ፣ የዐርሽ ተሸካሚ የሆኑ መልአክቶቹ፣ የተቀሩትም ሰማይ ውስጥ የሚኖሩ መልአክቶች፣ በምድር የሚኖሩ ሰዉም ጂንም አጠቃላይ እንስሶችም፣ ጉንዳን እንኳን ከምድር በታች ባለው ቤቷ ሳይቀር፣ አሳና የባህር እንስሶችም ሳይቀሩ የየብሱም ይሁን የባህሩ እንስሶች ባጠቃላይ እነዚህ ሁሉ መዳኛቸውና መድህናቸው የሆነውን መልካም ነገርና ሃይማኖታዊ ትምህርቶችን ለሚያስተምር ሰው ዱዓ ያደርጋሉ።