ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ዱዓቸውን ጥግ ከማድረሳቸው የተነሳ አፍንጫውን አፈር ላይ እንደተደፋ ሰው በማድረግ በውርደት እንዲከናነብ ሶስት ጊዜ ረገሙት። የአላህ መልክተኛ ሆይ! ማንን ነው የረገሙት? ተብለው ተጠየቁ። ነቢዩም (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) አንዳቸውን ወይም ሁለቱን ወላጆቹ በእርጅና ወቅት አግኝቶ እነርሱ ጀነት ለመግባቱ ሰበብ ያልሆኑት ነው አሉ። ይህም የሚሆነው ለነርሱ በጎ ባለማድረጉና ሐቃቸውን በመንፈጉ ምክንያት ነው።