ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ከሰዎች ሁሉ አስበልጠን በጎ ሊዋልለት፣ መልካም ሊሰራለት የሚገባው፣ ባማረ መልኩ ልንኗኗረው፣ ልንወዳጀውና ትስስራችንን ልናጠናክርለት የሚገባው በላጩ ሰው ማን እንደሆነ ገለፁ። እርሷም እናት ናት። ከሌሎች አካላቶች ሐቅ የእናት ሐቅ የበለጠ እንደሆነ ለማስገንዘብም ሶስት ጊዜ በመደጋገም አጽንዖት ሰጡት። ይህም የርሷ ደረጃ ከተቀሩት ሰዎች ባጠቃላይ እንደሚበልጥ ለመግለፅ ነው። ቀጥለውም ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ከእናት በመቀጠል በጎ ሊዋልለት የሚገባውን እንዲህ በማለት ገለፁ: ቀጥሎ አባት ቀጥሎ ቅርብ የሆኑ ዘመዶች አሉ። እጅግ ቅርብ በሆነ ቁጥር ሩቅ ከሆነው ዘመድ የበለጠ ዝምድናው ሊቀጠል ይገባል።