explain-icon

ትንታኔ

ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና አላህ አምልኮና ህግጋቶቹን በማቅለል የደነገጋቸው ማግራሪያዎች ሲተገበሩ እንደሚወድ ተናገሩ። እንዲሁም አቅመ አዳምና ጤነኛ የሆኑ ሰዎች በተቸገሩ ሰዓት የደነገገላቸውን ማቅለያዎች ለምሳሌ፦ ጉዞ ላይ ሰላትን ማሳጠርና ሰላትን ሰብስቦ መስገድ ይመስል ሲፈጸሙም አላህ እንደሚወድ ተናገሩ። ይህም ልክ ግዴታ ያደረጋቸው ሲሰሩ (ተግባራዊ ሲደረጉ) እንደሚወደው ነው። ምክንያቱም አላህ ባግራራውም ጉዳዮች ሆነ ግዴታ ባደረገው ጉዳዮች ላይ ትእዛዙ አንድ ነውና።

explain-icon

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  • ጥራት የተገባው አላህ የደነገጋቸው ማግራሪያዎች ሲሰሩ መውደዱ አላህ በባሮቹ ላይ ያለውን እዝነት እንረዳለን።
  • የዚህን ሸሪዐ ምሉእነትና በሙስሊም ላይ ችግርን ያነሳ መሆኑን እንረዳለን።