አንድ ሰውዬ ወደ ነቢዩ - የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - ዘንድ በመምጣት እንዲህ አለ: "የአላህ መልክተኛ ሆይ! አንድ ሰው ገንዘቤን ለመውሰድ ፈልጎ ቢመጣ ምን ማድረግ እንዳለብኝ እስኪ ንገሩኝ?" እርሳቸውም "ገንዘብህን መስጠት አይጠበቅብህም" አሉት። እርሱም "ከተጋደለኝስ?" አላቸው። እርሳቸውም "አንተም ተጋደለው።" አሉት። እርሱም "እርሱ ቢገለኝስ?" አላቸው። እርሳቸውም "አንተ ሰማዕት ነህ።" አሉት። እርሱም "እኔ ብገለውስ?" አላቸው። እርሳቸውም "እርሱ የትንሳኤ ቀን በእሳት ውስጥ ለመቀጣት የተገባ ነው።" አሉት።