ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ትናንሽ ተደርገው የሚታዩ ወንጀሎችን መስራት ላይ ከመዘናጋትና አብዝቶ ከመስራት አስጠነቀቁ። ትናንሽ ወንጀሎች ተሰባስበው ባለቤቱን ያጠፋሉና። ለዚህም ወደ ሸለቆ ውስጥ የወረዱ ሰዎችን ምሳሌ አደረጉ። ሁሉም ያመጧቸው ትናንሽ እንጨቶች ተጠራቅመው ዳቦዋቸውን ለመጋገር እስኪያስችሏቸው ድረስ እያንዳንዳቸው ትናንሽ እንጨት ይዘው መጡ። ትናንሽ ወንጀሎችም ሰውዬው ሳይቶብት ወይም ከነርሱ አላህ ይቅር ሳይለው በነርሱ ምክንያት የተያዘ ጊዜ ያወድሙታል።