ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ከሰዎች ሁሉ እጅግ በጣም ቸር ነበሩ። ለሚገባው የሚገባውን በመስጠት ቸርነታቸው የሚበዛውም በረመዷን ወር ነበር። የቸርነታቸው መጨመር ምክንያትም ሁለት ነገሮች ናቸው: የመጀመሪያው: ጂብሪልን ዐለይሂ ሰላም ማግኘታቸው ሲሆን፤ ሌላኛው ደግሞ: ቁርአንን መማማራቸው ነው። ማለትም ከቀልባቸው በሽምደዳ መቅራታቸው ማለት ነው። ጂብሪል ዐለይሂ ሰላም በርሳቸው ላይ የወረደውን ቁርአን ባጠቃላይ ያስተምራቸዋል። የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እጅግ ቸር፣ አብዝቶ ሰጪ፣ መልካም ተግባሪና አላህ በዝናብና በእዝነት ከሚልካት መልካም ንፋስ የበለጠ ለፍጡራን ፈጥኖ ደራሽ ነበሩ።