አቡቀታዳህ አልአንሷሪይ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - ከርሱ ይደበቅ የነበረን ተበዳሪን ይፈልግ ነበርና አገኘው። ተበዳሪውም እንዲህ አለው "እኔ ችግርተኛ ነኝ። እዳህን የምከፍልበት ገንዘብም የለኝም።" አቡቀታዳህም (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - ገንዘብ እንደሌለው ምሎ እንዲነግረው ጠየቀው። በሚናገረው ነገር እውነቱን እንደሆነም በአላህ ምሎ ነገረው። አቡ ቀታዳህም (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ሲሉ እነደደሰማ ተናገረ: አላህ ከትንሳኤ ቀን ችግሮችና ጭንቆች እንዲያድነው ያስደሰተው ሰው ከችግርተኛ ያቅልል። ይህም መክፈያ ጊዜውን በማዘግየትና በማርዘም ወይም የተወሰነውን እዳ ወይም ሁሉንም ይቅር በማለት ነው።