explain-icon

ትንታኔ

ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ውዱእን ሱናዎቹና አዳቦቹን ከመጠባበቅ ጋር ያደረገ ሰው ይህ ውዱኡ ወንጀሎቹ ከእጆቹና እግሮቹ ጣቶች ስር ጭምር እስኪወጡ ድረስ ወንጀሎቹ እንዲማሩና ሀጢአቶቹ እንዲረግፉ ከሚያደርጉ ምክንያቶቹ አንዱ መሆኑን እየነገሩን ነው።

explain-icon

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  • ውዱእን ሱናዎቹንና አዳቦቹን ተምሮ በመተግበር ላይ ትኩረት እንድናደርግ መነሳሳቱን እንረዳለን።
  • የውዱእን ትሩፋት እንረዳለን። ውዱእ ትናንሽ ወንጀሎችን የሚያስምር ነው። ትላልቅ ወንጀሎች ግን የግድ ተውበት ያስፈልጋቸዋል።
  • ወንጀሎች ከሰውነታችን እንዲወጡ ውዱእን ማሟላቱና ያለምንም ጉድለት ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንደገለፁት መፈፀሙ መስፈርት ነው።
  • እዚህ ሐዲሥ ውስጥ የተጠቀሰው ወንጀሎችን ማስማር ትላልቅ ወንጀሎችን በመራቅና ከርሱ ተውበት በማድረግ ላይ የተገደበ ነው። አላህ እንዲህ ብሏልና {ከእርሱ ከተከለከላችሁት ታላላቆቹን (ሀጢአቶች) ብትርቁ (ትናንሾቹን) ሀጢአቶቻችሁን ከእናንተ እናብሳለን።} [አንኒሳእ:31]