ዐምር ቢን ዓሚር ከአነስ ቢን ማሊክ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንዳስተላለፈው እንዲህ አሉ፦ "ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) በሁሉም ሶላት ወቅት ዉዱእ ያደርጉ ነበር። 'እናንተስ እንዴት ነበር የምታደርጉት?' አልኩኝ። አነስም 'ዉዱእ እስካላጠፋን ድረስ (የነበረን) ዉዱእ ይበቃን ነበር።' አለ።" ሶሒሕ ነው። - ቡኻሪ ዘግበውታል።