ነቢዩ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- እንዲህ በማለት ተናገሩ። አላህ ብዙ ነገሮችን ግዴታ አድርጓልም ደንግጓልም። አጥብቃችሁ ያዙት፤ በመተው ወይም በመዘናጋት እንዳታጓድሉት። አላህ እናንተን የሚያቅቡና እርሱ ከማይወደው የሚያግዷችሁን የተወሰኑ ማቀቢያዎችንና ማገጃዎችን አድርጓልና በሸሪዓ ካዘዘው አትለፉ። አላህ ውግዝ ነገሮችን ስለከለከለ አትፈፅሟትም አትቅረቧትም። ከነዚህ ውጪ ያሉን ግን ለባሮቹ በማዘን ትቷቸዋል ዝምም ብሏቸዋል። ልክ በመሰረቱ እንደነበረው ፍቁድ እንደሆነ ይቀራል። ስለርሱም አትፈላፈሉ።