ነቢዩ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- እንደዝሙትና ስርቆት የመሰሉ ሸሪዓዊ የምድር ቅጣቶችን የሚያስፈርዱ ወንጀሎችን የፈፀመ ሰውና ቅጣቱን በምድር መቅጫ ሸሪዓው ህግ መሰረት የተቀጣ ይህ መቀጣቱ የተቀጣባትን ወንጀል እንደሚያብስለት፤ በመጪው አለም ያለበትንም ቅጣት እንደሚያስነሳለት ተናገሩ። ምክንያቱንም ሲገልፁ አላህ በባሪያው ላይ ሁለት ቅጣቶችን ሰብስቦ ከመቅጣት የላቀ አዛኝና ቸር ነው አሉ። አላህ በዱንያ ወንጀሉን የሸሸገለት፤ በዛ ወንጀሉም ያልቀጣው፤ አላህ ይቅር ያለውና የማረው ሰውም አላህ ዐዘ ወጀል የማረውንና ይቅር ያለውን ወንጀል ወደ ኋላ ተመልሶ ከመቅጣትም የላቀ የተከበረና ቸር ነው አሉ።