አቡሰዒድ አልኹድሪይ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ሳታገባና ወንዶች ጋር ሳትኗኗር በቤቷ ተሸሽጋ ከምትኖር ልጃገረድ ሴት የበለጠ አይነአፋር እንደነበሩ ተናገረ። እጅግ አይነአፋር ከመሆናቸው የተነሳ አንድ ነገር የጠሉ ጊዜ ፊታቸው ይለዋወጣል እንጂ አይናገሩም። ይልቁኑም ባልደረቦቻቸው ፊታቸውን በመመልከት ያንን ነገር መጥላታቸውን ይረዳሉ።