ከሐሰን እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «ጁንዱብ ቢን ዐብደላህ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እዚሁ መስጂድ ውስጥ ነገሩን። ከነገሩን ጀምሮም አልረሳነውም። ጁንዱብም በአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ላይ ዋሽቷል ብለንም በፍፁም አንፈራም። እንዲህም አሉ: "የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እንዲህ ብለዋል: "ከናንተ በፊት ከነበሩት ህዝቦች መካከል አንድ የቆሰለ ሰውዬ ነበር። ትእግስት በማጣቱም ቢላ አንስቶ እጁን ቆረጠ። እስኪሞት ድረስም ደሙ አልተቋረጠም። አላህም እንዲህ አለ: 'ባሪያዬ ነፍሱን በማውጣት ተቻኮለኝ። በርሱ ላይም ጀነትን እርም አድርጌበታለሁ።' " ሶሒሕ ነው። - ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።