ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) የሐርን ልብስ በየትኛውም አይነቱ ከመልበስ ወንዶችን ከለከሉ። ወንዶችንም ሴቶችንም በወርቅና ብር እቃዎችና መሳሪያ ከመብላትና ከመጠጣት ከለከሉ። ይህም አማኞች በዚህች አለም አላህን ለመታዘዝ እንደራቁት ሁሉ የትንሳኤ ቀን ደግሞ ለአማኞች ብቻ እንደሆነ ተናገሩ። ከሀዲያኖችስ በመጪው ዓለም ምንም የላቸውም። ምክንያቱም የአላህን ትእዛዝ በማመፅ ቸኩለው በዚህ ዓለም ህይወታቸው ምርጥ የሚሉትን ነገሮች በመያዝ ስለተጠቀሙ ነው።