ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) አንድ ወንድ ሙስሊም ሽርጡን ምን ማድረግ እንዳለበት ገለፁ። ሽርጥ ሲባል (በዚህ አገባቡ) የወንድን ከወገብ በታች የሚሸፍን የሆነ ልብስ ሁሉ የሚመለከት ነው። ይህም ሶስት ሁኔታዎች አሉት: የመጀመሪያው: ተወዳጅ የሆነ ነው። ይህም እስከ ባቱ ግማሽ ድረስ አሳጥሮ ማድረግ ነው። ሁለተኛው: ሳይጠላ የሚፈቀድ ነው። ይህም ከባቱ ግማሽ በታች እስከ ቁርጭምጭሚቱ ድረስ ባለው አሳጥሮ ማድረጉ ነው። ቁርጭምጭሚት ማለት በባትና እግር መካከል የሚለየው እብጥ ያሉት አጥንቶች ናቸው። ሶስተኛው: ክልክል የሆነው ነው። ይህም ከቁርጭምጭሚት በታች መሆኑ ነው። ይህም እሳት እንዳያገኘው ይፈራለታል። ከቁርጭምጭሚቱ በታች ያስረዘመው በኩራት፣ በመመፃደቅና በጥመት ከሆነ ደግሞ አላህ ወደርሱ አይመለከትም።