explain-icon

ትንታኔ

ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ከሳቸው በኋላ በወንዶች ላይ ከሴቶች የበለጠ እጅግ ጎጂ ፈተናና መሞከሪያ እንዳልተዉ ተናገሩ። ወንዶች በሴቶች መጎዳታቸው ሴቷ ከቤተሰቡ አባላት ከሆነች ሸሪዓን በሚፃረር ጉዳይ እሷን በመከተል ይከሰታል። ባዳ ከሆነች ደግሞ ከሷ ጋር በመቀላቀልና ለብቻቸው በመገለል በርሱ ሳቢያ ብልሽቶችን የሚያመጡ ነገሮችን በመፈፀም ነው።

explain-icon

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  • ሙስሊም የሆነ ሰው የሴቶችን ፈተና መጠንቀቅና በርሷ ወደ መፈተን የሚያደርሰውን መንገዶችን ሁሉ መዝጋት ይገባዋል።
  • አንድ አማኝ በአላህ መጠበቅና ከፈተና ነፃ እንዲያደርገውም ወደርሱ መከጀል ይገባዋል።