explain-icon

ትንታኔ

ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እየነገሩን ያሉት ዝምድናን በመቀጠል የተሟላና ለዘመዶቹም በጎ ሰሪ የሚባለው ላደረጉለት መልካም ነገር መልካሙን በመመለስ ብቻ የተቆጠበ አይደለም። ይልቁንም ዝምድናውን በመቀጠል በኩል የተሟላ የሚባለው ዝምድናው በተቆረጠ ጊዜ የሚቀጥል፤ ሰዎቹ እያስከፉትም ለነርሱ መልካሙን በማድረግ ምላሽ የሚሰጣቸው የሆነ ነው።

explain-icon

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  • ዝምድናን መቀጠል ሲባል በሸሪዓ የሚፈለግበት ካንተጋ የተቆራረጡትን ስትቀጥል፤ የበደሉህን ይቅር ስትላቸው፤ የነፈጉህን ስትለግሳቸው እንጂ ብድር በመመለስ መልኩ ላደረጉልህ ነገር ተመሳሳዩን ምላሽ መስጠትህ አይደለም።
  • ዝምድናን መቀጠል የሚፈፀመው በገንዘብ፣ በዱዓእ፣ መልካሙን በማዘዝና ከመጥፎ በመከልከል ረገድ እና መሰል በሆኑ ነገራቶች ለነርሱ በጎ በማድረግ እንዲሁም ክፋትን ከነርሱ በተቻለ መጠን በማስወገድ ነው።