አነስ ቢን ማሊክ -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና- እንዳስተላለፉት እንዲህ አሉ: «የአላህ መልክተኛ - የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - እንዲህ ብለዋል፦ "ወንድምህ በዳይም ሆነ ወይም ተበዳይ እርዳው።" አንድ ሰውዬም እንዲህ አለ: "የአላህ መልክተኛ ሆይ! ተበዳይ የሆነ ጊዜ እረዳዋለሁ። እስኪ ንገሩኝ በዳይ በሆነ ጊዜ እንዴት ነው የምረዳው?" እርሳቸውም "ከመበደል ታቅበዋለህ ወይም ትከለክለዋለህ። ይህ እርሱን መርዳት ነው።" ብለው መለሱ።» ሶሒሕ ነው። - ቡኻሪ ዘግበውታል።
explain-icon

ትንታኔ

ነቢዩ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ሙስሊም ወንድም በዳይም ሆነ ወይም ተበዳይ እንዲረዳ አዘዙ። አንድ ሰውዬም እንዲህ አለ: የአላህ መልክተኛ ሆይ! ተበዳይ በሆነ ጊዜ በደልን ከርሱ ላይ በማስወገድ እረዳዋለሁ። ንገሩኝ እስኪ በዳይ ከሆነ እንዴት ነው የምረዳው? እርሳቸውም እንዲህ በማለት መለሱ: ከበደል ትከለክለዋለህ፣ እጁን ትይዘዋለህ፣ ትገታዋለህ፣ ታቅበዋለህ። ይህ በሰይጣኑና በመጥፎ በምታዘው ነፍሱ ላይ እያገዝከው ነው።

explain-icon

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  • በሙስሊሞች መካከል የእምነታዊ ወንድማማችነት ሀቆች መካከል አንዱን ሀቅ ተገንዝበናል።
  • የበዳይን እጅ መያዝና ከበደል መከልከል እንደሚገባ እንረዳለን።
  • ተበዳዮች ሁነውም ይሁን በዳይ ሁነው እርስ በርስ ይረዳዱ የነበሩትን የድንቁርና አስተሳሰብ እስልምና ተፃሮ መምጣቱን እንረዳለን።