አቡቡርዳህ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - አባቱ አቡ ሙሳ አልአሽዐሪይ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - ከባድ በሽታ እንደታመመና ራሱን እንደሳተ ተናገረ። ጭንቅላቱም ባለቤቱ ታፋ ላይ ነበር። እርሷም እየጮኸች ሙሾ አወረደች። ራሱን ስቶ ስለነበረ አንዳችም ሊመልስላት አልቻለም ነበር። የነቃም ጊዜ እንዲህ አለ: የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ራሳቸውን ካጠሩት ሁሉ እኔም አጥርቻለሁ። ነቢዩ: (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ከነዚህ ራሳቸውን አጥርተዋል: ከ "ሷሊቃህ": በመከራ ወቅት ድምጿን ከፍ ከምታደርግ፤ ከ "ሓሊቃህ": በመከራ ወቅት ፀጉሯን ከምትላጭ፤ ከ "ሻቃህ": በመከራ ወቅት ልብሷን ከምትቀዳድ የጠራሁ ነኝ ብለዋል። እነዚህ ነገሮች የድንቁርናው ዘመን መገለጫ ስለሆኑ ነው። ይልቁንም በመከራ ወቅት ትእግስት በማድረግና ምንዳውን አላህ ዘንድ በማሰብ አዘዙ።