ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ሙእሚን ሁሉ ነገሩ መልካም እንደሆነ፤ ነገር ግን በኢማኑ፣ በቆራጥነቱ፣ በገንዘቡም በሌላም የኃይል ጎን ጠንካራ የሆነው ሙእሚን ከደካማው ሙእሚን የበለጠ አላህ ዘንድ ምርጥና ተወዳጅ መሆኑን ገለፁ። ቀጥለውም ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) አማኝ ለሆነ ሰው ጥራት በተገባውና ከፍ ባለው አላህ ላይ ከመመካትና ከመታገዝ ጋር ለዱንያዊም ይሁን ለአኺራዊ ጉዳዮቹ የሚጠቅመውን ሰበቦች መያዝ እንደሚገባው መከሩ። ቀጥለው ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ለሁለቱ ዓለም የሚጠቅሙ ነገሮችን ከመተግበር መዳከም፣ መታከትንና መሳነፍን ከለከሉ። አማኝ የሆነ ሰው በአላህ በመታገዝ በአንድ ስራ ላይ ከታገለ፣ ሰበቦችን ከያዘና ከአላህ መልካሙን ከፈለገ በኋላ ሁሉን ነገሩ ወደ አላህ ማስጠጋትና የአላህ ምርጫ የተሻለ መሆኑን ማወቅ እንጂ ሌላ ጣጣ ውስጥ መግባት የለበትም። ከዚህም በኋላ አንድ ችግር ቢያገኘው እንዲህ ማለት የለበትም: "እንዲህ ባደርግ ኖሮ እንዲህ እንዲህ ይሆን ነበር።" ""እንዲህ ባደርግ ኖሮ" ማለት የአላህን ውሳኔ በመቃወም፣ ባለፈ ነገር በመቆጨት፣ የሰይጣንን ስራ ትከፍታለች። ነገር ግን በመቀበልና በመውደድ "ይህ የአላህ ውሳኔ ነው። አላህም የፈለገውን ፈፀመ።" ይበል። የተከሰተው ነገር አላህ በፈለገው መሰረት ነው። እርሱ የፈለገውን ነገር ፈፃሚ ነው፤ የርሱን ውሳኔ መላሽ የለም፤ ፍርዱንም የሚያቅብ የለም።