ከአቡ ሁረይራ (ረዲየላሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው : ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል: "ፀሀይ ከወጣችባቸው ቀናቶች ሁሉ በላጩ ቀን የጁመዓ ቀን ነው። በዚህ ቀን ኣደም ተፈጠረ፣ በዚሁ ቀን ጀነት ገባ፣ በዚሁ ቀን ከርሷ ወጣ፣ ሰአቲቱም በጁመዓ ቀን ካልሆነ በቀር አትከሰትም።" ሶሒሕ ነው። - ሙስሊም ዘግበውታል።