ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) የሸሪዓ ድንጋጌዎች ለሶስት እንደሚከፈሉ ገለፁ። እነሱም: ዝም የተባለ፣ ክልከላዎችና ትእዛዛት ናቸው። የመጀመሪያው: አላህና ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ስለርሱ ዝም ያሉት ነው። ፍርድ ከሌለው የነገሮች መሰረቱ ግዴታ አለመሆኑ ነው። በርሳቸው ዘመን ስለአንዳች ስላልተከሰተ ነገር መጠየቅን መተው ግዴታ ነበር። ይህም በርሳቸው ላይ ግዴታ የሚያደርግ ወይም ክልክል የሚያደርግ መመርያ እንዳይወርድ ነው። አላህ የተዋት ለባሮቹ በማዘኑ ነውና። እርሳቸው (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ከሞቱ በኋላ ግን ጥያቄው ፈታዋ በመጠየቅ መልኩ ወይም በሃይማኖቱ ጉዳይ የሚያስፈልገውን በመማር መልኩ የቀረበ ከሆነ ይህ የተፈቀደ ብቻ ሳይሆን የታዘዘበትም ጭምር ነው። ጥያቄን የጠየቀው ተጨንቆ ፈጥሮና በግትርነት ከሆነ ግን እዚህ ሐዲሥ ውስጥ መጠየቅን በመተው የተፈለገው ይህ አይነቱን ነው። ይህም በኒ ኢስራኤሎች ላይ የተከሰተው አምሳያ ወደመከሰት ስለሚያመራ ነው። ይህም ላም እንዲያርዱ በታዘዙ ወቅት ማንኛውንም የላም አይነት ቢያርዱ ትእዛዙን እንደፈፀሙ ይቆጠርላቸው ነበር። ነገር ግን እነሱ በመጠየቅ ሲያጠብቁት ትእዛዙም ጠበቀባቸው። ሁለተኛው: ክልከላዎች ናቸው: ይህም መተዉ የሚያስመነዳ መተግበሩ የሚያስቀጣ ነው። ይህንንም ሙሉ ለሙሉ መራቅ ግዴታ ነው። ሶስተኛው: ትእዛዝ ነው። እርሱም መስራቱ የሚያስመነዳ መተዉ የሚያስቀጣ ነው። በአቅም ልክ መተግበሩም ግዴታ ነው።