ኡሙ ዐጢየህ አልአንሷሪየህ (አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና) ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ሴቶች ጀናዛን ለመሸኘት አብረው ከመሄድ እንደተከለከሉ ተናገረች። ይህም ለነርሱም ይሁን በነርሱ ምክንያት ፈተና ይከሰታል ተብሎ ስለተፈራና ትእግስታቸው ያነሰ ስለሆነ ነው። ቀጥላም (አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና) ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ሌሎች ክልከላዎች ላይ እንደሚያከብዱት ይህንን ግን ክብደት ሰጥተው አልከለከሉም አለች።