ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) አማኝ የሆነ ወንድና ሴት ባሪያ ከፈፀማቸው ሁሉም ወንጀሎችና ኃጢዐቶች የፀዳ ሆኖ አላህን እስኪገናኝ ድረስና በነዚህ መከራዎች ሁሉንም ወንጀሎቹን አላህ እስኪምረው ድረስ በነፍሱ (በጤናውና በአካሉ)፣ በልጆቹ (በህመም ወይም ሞት ወይም በነርሱ በመበደል ወይም ከዚህ ውጪ ባሉ በልጆች ሳቢያ በሚደርሱ መከራዎች)፣ በገንዘቡ (በመደኽየት፣ ንግዱን በመክሰር፣ በመሰረቅ፣ በኑሮ መወደድ፣ በሲሳይ መጥበብ) የሚያጋጥመው መከራና ፈተና አይላቀቀውም ብለው ተናገሩ።