የተወሰኑ ሶሐቦች - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ቤት ውስጥ በድብቅ ስለሚሰሩት ዒባዳ ለመጠየቅ ወደ ሚስቶቻቸው ቤት መጡ። የርሳቸው የቤት ውስጥ አምልኮ ሲነገራቸውም የራሳቸውን ስራ አሳንሰው ተመለከቱና እንዲህ አሉ: "እኛ ከነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) አንፃር የት ነን? ለርሳቸው ያሳለፉትንም ሆነ የሚመጣውን ወንጀል ተምረዋል። እኛስ ከርሳቸው ተቃራኒ ምህረት ማግኘታችንን እንኳ አላወቅንም። ስለዚህ ይህን የአላህ ምህረት ለማግኘት አምልኳችን ከገደብ ያለፈ መሆን አለበት።" ቀጥለውም አንዱ "እኔ ሴት አላገባም!" አለ። ሁለተኛው ደግሞ "እኔ ስጋ አልበላም!" አለ። ሌላኛው ደግሞ "እኔ ፍራሽ ላይ አልተኛም።" አለ። ይህ ንግግራቸውም ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ዘንድ ደረሰና ተቆጡ። ለሰዎችም ኹጥባ አደረጉ። አላህን አመስግነው ካወደሱ በኋላ እንዲህ አሉ: "እንዲህ እንዲህ ያሉ ሰዎች ምንድነው ጉዳያቸው? ወላሂ እኔ ከሁላቹም እጅግ አላህን ፈሪውና ተጠንቃቂው ነኝ። ነገር ግን እኔ ሌሊት ለመቆም እንድበራታ እተኛለሁ፤ ለጾም እንድበራታም አፈጥራለሁ፤ ሴትንም አገባለሁ። ከኔ መንገድ አፈንግጦ ከኔ መንገድ ውጪ የተሟላ መንገድ እንዳለ የተመለከተና ከኔ መንገድ ውጪ የያዘ ሰው ከኔ አይደለም።"