ከአማኞች እናት ዓኢሻ (ረዲየሏሁ ዐንሃ) - አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና - እንደተላለፈው እንዲህ ብላለች፦ «ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ጫማ ሲለብሱ፣ ሲያበጥሩ፣ ሲፅዳዱና በሁሉም ጉዳያቸው ቀኝን መጠቀም ይወዱ ነበር።» ሶሒሕ ነው። - ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።