የአማኞች እናት ዓኢሻ - አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና - ዘንድ ሐውላእ ቢንት ቱወይት - አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና - ነበረች። ነቢዩ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - ሲገቡ እርሷ ወጣች። ዓኢሻም እንዲህ አለቻቸው: ይህቺ ሴት ሌሊት አትተኛም። ይልቁንም ሌሊቱን በሙሉ የምታሳልፈው በሶላት ነው። ነቢዩም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - በራሷ ላይ ማክበዷን በማውገዝ እንዲህ አሉ: ሌሊት አትተኛም?! ከመልካም ስራ መዘውተር የምትችሉትን ያህል ብቻ በመስራት ተጠመዱ። በአላህ እምላለሁ! አላህ ባሮቹ ስራን ከመስራት እስኪሰለቹ እና እስኪተዉ ድረስ ለደጋግና ታዛዥ ባሮቹ በአምልኳቸው፣ በመልካምና በጎ ስራዎቻቸው ምንዳና አጅር ከመስጠት አይሰለችም።