አንድ ሰውዬ ቅርብ ዘመዶች እንዳሉትና ከነርሱም ጋር በመልካም መስተጋብር እንደሚኗኗር እነርሱ ግን ከዚህ ተቃራኒ በሆነ መንገድ እንደሚኗኗሩት ለነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ስሞታ አቀረበ። እርሱ ይቀጥላቸዋልም፤ ይጠይቃቸዋልም፤ እነርሱ ግን ይቆርጡታል። በበጎነትና በታማኝነት ለነርሱ መልካም ቢውልም እነርሱ ግን በግፍና በድርቅና መጥፎ ይሰሩበታል። ይታገሳቸዋልም፤ ይቅር ይላቸዋልም፤ እነርሱ ግን በፀያፍ ንግግርና ተግባር ይቅርታውን ችላ ይላሉ። ከነዚህ ከተጠቀሱት ተግባራቸው ጋር ዝምድና መቀጠሌን ልግፋበትን? ነቢዩም (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ለርሱ እንዲህ አሉት: እንዳወሳኸው ከሆነ አንተ ራሳቸውን እንዲያዋርዱና እንዲንቁ ነው ያደረግካቸው። በጎ መዋልህ በዝቶላቸው የነርሱ ነፍስ ግን ፀያፍ ተግባር ብቻ መስራቱ ልክ ትኩስ አመድ እንዳበላሀቸው ነው። አንተ ባወሳህልኝ በጎ መዋል ላይ እስከዘወተርክና እነርሱም ላንተ መጥፎ ማድረግ ላይ እስከዘወተሩ ድረስ በነርሱ ላይ የሚያግዝህና የነርሱን ማወክ የሚከላከልልህ ከአላህ ዘንድ የሆነ አጋዥም ከአንተ አይወገድም።