ከኢብኑ መስዑድ - አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ ብለዋል፡- «ጉዞ ላይ ከአላህ መልክተኛ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - ጋር ነበርን። እርሳቸው ለመፀዳዳት ሄዱ። እኛም ትንሽዬን ወፍ ከነሁለት ጫጩቶቿ ተመለከትንና ጫጩቶቿን ወሰድን። ወፏም ክንፏን እያራገበች በራ መጣች። ነቢዩም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - እንዲህ አሉ: "ይህቺን ወፍ ልጆቿን ወስዶ ያስደነገጣት ማነው? ልጆቿን መልሱላት።" ጉንዳኖች ወረውት በእሳት ያቃጠልነውን ስፍራም ተመልክተው እንዲህ አሉ: "ይህንንስ ያቃጠለው ማነው?" እኛም "እኛ ነን።" አልን። እርሳቸውም: " እነሆ የእሳት ጌታ ካልሆነ በቀር ማንም በእሳት መቅጣት አይገባውም።" አሉ።» ሶሒሕ ነው። - አቡዳውድ ዘግበውታል።
explain-icon

ትንታኔ

ዐብደላህ ቢን መስዑድ - አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና - እንዳወሱት ጉዞ ላይ ከነቢዩ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - ጋር ሳሉ ነቢዩ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - ለመፀዳዳት ሄዱ። ሶሓቦችም ትንሽዬ ወፍ ከነሁለት ጫጩቶቿ አገኙና ጫጩቶቹን ይዘው ሄዱ። ወፏም ጫጩቶቿን በማጣት ድንጋጤ ክንፏን እያራገበችና ዘርግታ እየበረረች መጣች። ነቢዩም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - መጡና እንዲህ አሉ: ማነው ልጆቿን በመውሰድ ያሳዘናትና ያስፈራራት? ቀጥሎ እንዲመለሱላት አዘዙ። ቀጥለው በእሳት የተቃጠለ ጉንዳኖች የወረሩት ስፍራ ተመለከቱ። ነቢዩም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - "ማነው ይህንን ያቃጠለው?" አሉ። አንዳንድ ሶሓቦችም "እኛ ነን።" አሉ። እርሳቸውም "እሳትን ከፈጠረው ከአላህ በቀር አንድም ሰው በህይወት ያለን በእሳት ሊቀጣ አይፈቀድለትም።" አሉ።

explain-icon

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  • ለመፀዳዳት ደበቅ ማለት የተደነገገ ተግባር እንደሆነ እንረዳለን።
  • እንስሳዎችን ልጆቻቸውን በመንጠቅ ከመቅጣት መከልከሉን እንረዳለን።
  • ጉንዳንና ነፍሳትን በእሳት ከማቃጠል መከልከሉን እንረዳለን።
  • ለእንስሳዎች በማዘንና በመራራት ላይ መነሳሳቱን እንረዳለን። በዚህም እስልምና ቀዳሚ መሆኑን እንረዳለን።
  • ነቢዩ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - ለእንስሳዎች የነበራቸው እዝነት መገለፁ፤
  • በእሳት መቅጣት አላህ ብቻ የተነጠለበት ጉዳይ እንደሆነም እንረዳለን።