ከዐብደላህ ቢን ዑመር (ረዲየሏሁ ዐንሁማ) -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: አንዲት ሴት ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) በተሳተፉበት አንድ ጦርነት ላይ ተገድላ ተገኘች። የአላህ መልክተኛም (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ሴትና ህፃናትን መግደልን አወገዙ። ሶሒሕ ነው። - ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
explain-icon

ትንታኔ

በአንድ ጦርነት ወቅት ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) አንዲት ሴት መገደሏን ተመለከቱ። እርሳቸውም የሴትንና ለአቅመ አዳም ያልደረሱ ህፃናት መገደልን አወገዙ።

explain-icon

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  • ከሴትና ከህፃናት ሆነው እንዲሁም እንደነሱ ደካሞች የሆኑ የጃጁ ሽማግሌዎችና ባህታዊዎች በስትራቴጂ እውቀታቸው ሙስሊሞችን በመዋጋት ላይ የሚያግዙ ካልሆኑ በቀር አይገደሉም። እንደዚህ ሆነው ከተገኙ ግን ይገደላሉ።
  • ሴቶችና ህፃናትን መግደል መከልከሉን እንረዳለን። ይህም እነዚህ አካላት ሙስሊሞችን ስለማይዋጉ ነው። በአላህ መንገድ የመታገል ዋነኛ አላማው የእውነት ጥሪ ወደ ሰዎች ባጠቃላይ እስኪደርስ ድረስ የሚያቅቡ አካላትን ሀይል መስበር ብቻ ነውና።
  • በዘመቻዎችና ጦርነቶች ሳይቀር የነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እዝነት ምን ያህል እንደነበር እንረዳለን።