ሑዘይፋ ቢን አልየማን (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - ከነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ጋር ሳለ ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) መሽናት ፈለጉና የቆሻሻ መጣያ ስፍራ ገቡ። የአብዛኛው ጊዜ ልማዳቸው ተቀምጦ መሽናት ቢሆንም ቆመው ሸኑ። ሑዘይፋም ከርሳቸው ራቅ አለ። ነቢዩም (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) "ቀረብ በል!" አሉት። ሑዘይፋም በዚህ ሁኔታ ላይ ሳሉ ከእይታ ሊጋርዳቸው ከኋላቸው ተረከዛቸው አጠገብ እስኪቆም ድረስ ቀረባቸው። ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ቀጥለው ዉዱእ አደረጉ። እግራቸውን የሚታጠቡበት ቦታ ላይ ሲደርሱም ኹፋቸውን ሳያወልቁ በላዩ ላይ በማበስ ብቻ ተብቃቁ። ኹፍ ማለት ከቀጭን ቆዳ ወይም ከመሳሰሉት የሚሰራ እግር ላይ የሚጠለቅና እስከ ቁርጭምጭሚት ድረስ የሚለበስ ካልሲ ነው።