ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) በአንድ ጉዟቸው ላይ ሳሉ ዉዱእ አደረጉ። ሁለት እግራቸውን ማጠብ ላይ በደረሱ ጊዜ ሙጊራ ቢን ሹዕባ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና እግራቸውን እንዲያጥቡ ብለው ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) አድርገውት የነበረውን ኹፍ ሊያወልቁ እጃቸውን ዘረጉ ነቢዩም (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) "አታውልቃቸው ተዋቸው! እኔ ሁለት እግሬን ኹፎቹ ውስጥ ያስገባሁት በጦሀራ ላይ ሁኜ ነው " አሏቸው። ነቢዩም (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እግራቸውን በማጠብ ምትክ ኹፋቸውን አበሱ።