ዑመር (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) አንድ ዉዱእ አድርጎ የጨረሰን ሰውዬ እግሩ ላይ ጥፍር የምታክል የዉዱእ ውሃ ያልነካት ስፍራን እንደተመለከቱበት ተናገሩ። ነቢዩም (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ወደ ተወው ስፍራ እየጠቆሙ እንዲህ አሉት: ተመለስና ዉዱእህን አሳምር! አሟልተህ አድርግ! ለሁሉም አካልህ ከውዱኡ ውሃ የሚገባውን ሐቅ ስጠው አሉት! ሰውዬውም ተመለሰና ዉዱኡን አሟልቶ ሰገደ።