explain-icon

ትንታኔ

ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) አብዝተው የሚፍቁና በመፋቅም ላይ የሚያዙ ነበሩ። አንዳንድ ወቅቶች ላይም አጠንክረው ሱናውን ይተገብሩ ነበር። ከነዛም ወቅቶች መካከል: ሌሊት በሚቆሙበት ወቅት መፋቅ ነው። ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) አፋቸውን በመፋቂያ ይፍቁና ያፀዱ ነበር።

explain-icon

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  • ከሌሊት እንቅልፍ በኋላ የመፋቅ ድንጋጌ አፅንዖት የተሰጠው መሆኑን እንረዳለን። ይህም እንቅልፍ የአፍ ጠረን እንዲለወጥ አንዱ ምክንያት ስለሆነ ነው። መፋቂያም የማፅጃ አንዱ መሳሪያ ነው።
  • የአፍ ጠረን ወደ መጥፎ ጠረን በሚለወጥበት ወቅት ባጠቃላይ መፋቅ አፅንዖት ተሰጥቶት የተደነገገ ጉዳይ መሆኑን እንረዳለን። ይህም ቀደም ተብሎ የተጠቀሰውን ሀሳብ በመያዝ ነው።
  • ጥቅል በሆነ መልኩ ፅዳት የተደነገገ ጉዳይ መሆኑን እንረዳለን። ንፅህና ከነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ሱናና ከምርጥ ስነ ምግባር አንዱ ነው።
  • አፍን ባጠቃላይ መፋቅ ሲባል ጥርሶችን፣ ድድንና ምላስንም ያካትታል።
  • መፋቂያ ማለት "አራክ" ከሚባል ዛፍ ወይም ከሌላ የዛፍ አይነት የሚቆረጥ እንጨት ነው። አፍንና ጥርስን ለማፅዳትም ያገለግላል። አፍን ያፀዳል፣ መጥፎ ጠረንንም ያስወግዳል።