ከሹረይሕ ቢን ሃኒእ እንደተላለፈው እንዲህ አለ: «እናታችን ዓኢሻን እንዲህ ብየ ጠየቅኳት: "ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ቤታቸው የገቡ ጊዜ በምን ነበር የሚጀምሩት?" እርሷም "በመፋቅ" በማለት መለሰችልኝ።» ሶሒሕ ነው። - ሙስሊም ዘግበውታል።
explain-icon

ትንታኔ

ከነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና መመሪያ መካከል በማንኛውም ወቅት በምሽትም ሆነ በቀን ቤታቸው የገቡ ጊዜ በመፋቂያ መጀመር አንዱ ነበር።

explain-icon

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  • በሁሉም ወቅት ባጠቃላይ መፋቂያ መደንገጉን እንረዳለን። ነቢዩ ይወደዳል ባሉበት ወቅት ደሞ ይበልጥ አፅንዖት ይሰጠዋል። ከነርሱም መካከል: ቤት በሚገባ ወቅት፣ ለሶላት በሚቆም ወቅት፣ ዉዱእ በሚደረግበት ወቅት፣ ከእንቅልፍ ከነቁ በኋላና የአፍ ጠረን በሚለወጥበት ወቅት ነው።
  • ታቢዒዮች እርሳቸውን ለመከተል ብለው ስለነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ሁኔታዎችና ሱናዎች በመጠየቅ ላይ የነበራቸው ጥረት እንረዳለን።
  • እናታችን ዓኢሻ (ረዺየሏሁ ዐንሃ) - አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና - ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ቤት በሚገቡ ወቅት ስለነበራቸው ሁኔታ መጠየቋ እውቀትን ከባለቤቱና በጉዳዩ እጅግ አዋቂ ከሆነው መውሰድ እንደሚገባ እንረዳለን።
  • ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ቤት በሚገቡ ወቅት አፋቸውን ማፅዳታቸው ሚስቶቻቸውን በመልካም መኗኗራቸውን ያስረዳናል።