የአላህ መልክተኛ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- የልጅ ልጅና መአዛቸው ከሆነው ከአቡ ሙሐመድ ሐሰን ቢን ዓሊይ ቢን አቢጧሊብ እንደተላለፈው እንዲህ አለ: «ከአላህ መልክተኛ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ይህንን ሸምድጃለሁ: "የሚያጠራጥርህን ነገር ተውና ወደ ማያጠራጥርህ ሂድ!" ሶሒሕ ነው። - رواه الترمذي والنسائي