ከአቡል ሐውራእ አስሰዕዲይ እንደተላለፈው እንዲህ አለ: ለሐሰን ቢን ዐሊይ (ረዲየሏሁ ዐንሁማ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - «ከአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ምን ሸምድደሃል? አልኩት። እርሱም: "ከአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ይህን ሸምድጃለሁ አለኝ። ‹የሚያጠራጥርህን ነገር ተውና ወደ ማያጠራጥርህ ሂድ! እውነት እርጋታን የተላበሰ ነው። ውሸት ደሞ ጥርጣሬን የተላበሰ ነው።›"» ሶሒሕ ነው። - رواه الترمذي والنسائي وأحمد