ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ከገድ እምነት አስጠነቀቁ። እርሱም: በሚሰማም ይሁን በሚታይ ነገር፤ በበራሪም ሆነ በእንስሳም ሆነ በህመምተኞች (አካል ጉዳተኞች)፤ በቁጥሮችም ሆነ በቀናት ወይም ከነዚህ ውጪ ባሉ ማንኛውም ነገርም ቢሆን ገደ ቢስነትን ማመን ነው። ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) በራሪን የጠቀሱት ጃሂሊዮች ዘንድ የታወቀ ስለሆነ ነው። የዚህ ስራ መሰረቱም ጉዞ ወይም ንግድ ወይም ከዚህ ውጪ ያሉ ስራዎችን ለመጀመር ሲሉ በራሪን ይለቁና ወደ ቀኝ አቅጣጫ ከበረረ ገድ አለኝ ብሎ ወደ ፈለገበት ጉዳይ ይሄዳል። ወደ ግራ አቅጣጫ ከበረረ ደግሞ ገደ ቢስ ነኝ ብሎ ያሰበውን ጉዳይ ከመፈፀም ይቆጠባል። ይህ ነገር ሺርክ መሆኑንም ተናገሩ። ገደቢስነትን ማመን ሺርክ የሆነውም መልካምን ከአላህ በቀር የሚያመጣ ስለሌለና፤ መጥፎንም ብቸኛና አጋር ከሌለው ከአላህ በቀር የሚከላከል ስለሌለ ነው። ኢብኑ መስዑድ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - በሙስሊም ቀልብ ውስጥ አንዳች ገደቢስ እምነት ሊከሰት እንደሚችል፤ ነገር ግን ሰበቡን ከማድረስ ጋር በአላህ ላይ በመመካት ማስወገድ እንዳለበት ገለፁ።