ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) በኡመታቸው ላይ እጅግ የሚፈሩት ነገር ትንሹን ሺርክ እንደሆነ እሱም ይዩልኝ እንደሆነ ተናገሩ። ይሀውም ለሰዎች ብሎ መስራቱ ነው። ቀጥለውም ለይዩልኝ የሚሰሩ ሰዎች የትንሳኤ ቀን የሚጠብቃቸውን ቅጣት ተናገሩ። ለነርሱ: "እነርሱ ዘንድ ምንዳን ታገኙ እንደሁ እስኪ በዱንያ ውስጥ ለይዩልኝ ወደምትሰሩላቸው ሂዱና ተመልከቱ? ለዚህ ስራችሁ ለናንተ መመንዳትና አጅር መስጠት ይችላሉን?" እንደሚባሉም ተናገሩ።